የኢትዮጵያ የስነ-ጥበብ እና የባህል ጥበቃ ፕሮግራም ተልዕኮ በኢትዮጵያ ያለውን አወንታዊ የጥበብ እና የባህል ውጤቶች ለተተኪው ትውልድ አሻራ ይሆን ዘንድ ለማስተላለፍ የጥበቃ ፕሮግራም በመቅረጽ ብቁ የሆነ የሰው ሀይል በተለያዩ የሙያ ዘርፎች ባለሙያዎችን ማፍራት ነው፡፡
download our proposalpreserve your heritage with us
በተትረፈረፈው የጥበብ እና የባህል፣የታሪክ፣የቱሪዝም ሀብት ባለቤት ሀገር ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት የሚል ስያሜ ቢሰጥ ማጋነን አይሆንም፡፡ በመሆኑም ያሉትን የጥበብ እና የባህል ሀብት ተግዳሮቶች ለመሙላት ይሄንን ፕሮግራም ቀርጸን በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፡፡ በኢትዮጵያ የጥበብና የባህል ጥበቃ ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሀይል አነስተኛ በመሆኑ፣አስፈላጊ የሆነ ቁሳቁስ ባለመኖሩ፣የተደራጁ ተቋማት ባለመኖራቸው ፣ ወጥ የሆነ መምሪያ ባለመኖሩ፣ሳይንሳዊ መንጎዶችን አለመከተል ዘርፉን በከፍተኛ ሁኔታ ወደ ኋላ አስቀርቶታል፡፡ ስለዚህ ይህ ፕሮግራም ከላይ የተጠቀሱትን ከፍተቶች ለመሙላት የወጣቶችን አቅም በማጎልበት የኢትዮጵያን የጥበብ እና የባህል ጥበቃ ድጋፍ ለማድረግ የተቋቋመ ፕሮግራም ነው፡፡ ይህን አላማ ለማሳካት በተመረጡት የሙያ ዘርፎች ማለትም፦ በዘመናዊ የአሳሳል ዘዴ ጥበቃ፣ የግድግዳ እና የሸራ ላይ ስዕሎችን መጠበቅ፣ የእደጥበብ ውጤቶችን መጠበቅ ሲሆን በዘላቂነት በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የኢትዮጵያ የጥበብና የባህል ሀብቶች ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ በመጀመሪያና በሁተኛ ዲግሪ ሙያተኞችን ማፍራት ነው ፡፡
መግቢያ
ተልዕኮ
ወርክ ሾፕ
-
የሸራና የግድግዳ ላይ ስዕሎችን መጠበቅ
Summer 2021
apply -
የወረቀት ስዕሎች ጥበቃ
Spring 2022
apply -
የወረቀት ስዕሎች ጥበቃ
Spring 2022
apply