የፕሮግራሙ አላማ
የኢትዮጵያ የስነ ጥበብና የባህል ጥበቃ ፕሮግራም የተቋቋመው ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ እና እድገቷን በቤሊጅየም ባደረገችው የዘመናዊ አሳሳል ጥበቃ ባለሙያ ናኦሚ ሙሌማን እና በኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ከአዲስ አበባ እና ባህዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው ፡፡ የፕሮግራሙ ዋና አላማ በቀጣይ አሰር አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት ዋና ዋና የስነ ጥበብ እና የባህል ውጤቶች ሳንሳዊ እውቀቶችን ከባህላዊ ጋር በማገናኘት ውድ እና ተተኪ የማይገኝላቸውን የሃገራችን የስልጣኔ መግለጫ የሆኑትን ሃብቶች ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ብቁ የሆኑ ሙያተኞች መፍጠር ነው፡፡ ይህን ለማሳካት ፕሮግራሙ ከሚመለከታቸው አካል ጋር በመሆን በሙያ ዘርፎቹ ላይ አትኩሮት ሰጥቶ የሚስራ ሲሆን በዘላቂየነት ራሱን የቻለ የስነ-ጥበብ እና የባህል ት/ት ቤት ማቋቋም ነዉ ፡፡
የፕሮግራሙ ዋና አላማ በቀጣይ አሰር አመታት በኢትዮጵያ ውስጥ ባሉት
ዋና ዋና የስነ ጥበብ እና የባህል ውጤቶች ሳንሳዊ እውቀቶችን ከባህላዊ ጋር
በማገናኘት ውድ እና ተተኪ የማይገኝላቸውን የሃገራችን የስልጣኔ መግለጫ
የሆኑትን ሃብቶች ለተተኪው ትውልድ ለማስተላለፍ ብቁ የሆኑ ሙያተኞች
መፍጠር ነው፡፡
ይህን ለማሳካት ፕሮግራሙ ከሚመለከታቸው አካል ጋር በመሆን በሙያ
ዘርፎቹ ላይ አትኩሮት ሰጥቶ የሚስራ ሲሆን በዘላቂየነት ራሱን የቻለ
የስነ-ጥበብ እና የባህል ት/ት ቤት ማቋቋም ነዉ ፡፡
instructors
ሰልጠኞች እና መረጣ
በዚህ ፕሮግራም ስር ለመሰልጠን የሚመለመሉ ተማሪዎች ሙያዊ ፍላጎታቸውን መሰረት በማድረግ የሚመለመሉ ይሆናል፡፡ በመጀመሪያው የሙከራ አመት 10-15 ሰልጣኞችን እንቀበላለን ፡፡ ፍላጎቱና ብቃቱ ያላቸው ሰልጣኞች በቀጠይ በሚዘጋጁ ወርክ ሾፖች መሳተፍ ይችላሉ፡፡ የመጀመሪያው ወርክሾፕ በታሪክዊቷ ከተማ ላሊበላ ይዘጋጃል ፡፡ ለዚህ ዝግጅት የተመለመሉ ከሌላ አከባቢ የሚገኙ ሰልጣኞች ላሊበላ ከተማ መገኘት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ማንኛውም ሰው ለመመዝገብ ሲፈልግ የሚያስፈልጉትን መመሪያዎች በማሟላት በውስጥ መስመር የሚመለከተውን አካል ጋር ግንኙነት በማድረግ መመዝገብ ይችላሉ፡፡